በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ አባላትና ወዳጆች፣ የቆመውን የአዳራሽ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ተባበሩን።
አሁኑኑ ይደግፉእርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
መዝሙረ ዳዊት 1፥3
ሰላምና የጌታ ጸጋ ይብዛላችሁ! እኛ የምሥራቅ ሾኔ አጥቢያ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላት ነን። ለብዙ ዓመታት እግዚአብሔርን ስናመልክ የኖርነው በእንጨት በተሠራች አነስተኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ነው። ዛሬ ግን ያ ሕንፃ እጅግ አርጅቷል። በአቅራቢያው በሚገኝ የሰው መኖሪያ ቤት ላይ የመውደቅ አደጋ ስላለው ለአባላቱም ሆነ ለጎረቤቶቻችን ሕይወት አስጊ ሆኗል። ከዚህም ሌላ የምዕመናኑ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመሄዱ ሕንፃው ሊይዘን አልቻለም። ብዙ ወንድሞችና እህቶች በአምልኮ ጊዜ ከቤት ውጭ ለመቆም ተገደዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት ሰፊና ትልቅ የአምልኮ አዳራሽ መገንባት ጀምረን ነበር። ሆኖም በድንገት የከተማው የኮሪደር ልማት ከህንፃው 4 ሜትር ያህል አፍርሷል። በዚህ ምክንያት ግንባታው ቆሟል። አሁን ሕንፃውን በተሻሻለ ዲዛይን አጠናቅቆ ለአገልግሎት ለማብቃት የእናንተ እገዛ ያስፈልገናል።
ድጋፍዎ የሚውልበት ቦታ፦ • የፈረሰውን የህንፃ ክፍል በተሻሻለው ዲዛይን መልሶ ለመሥራት • የግንባታ ቁሳቁስ (ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ቆርቆሮ ወዘተ) ለመግዛት • አዳራሹን አጠናቅቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ቅዱሳን፣ ወንድሞችና እህቶች፣ ወዳጆችም ሁሉ፦ ኑ ከጎናችን ቁሙ! ትልቅም ይሁን ትንሽ፣ እያንዳንዱ ስጦታ ለእግዚአብሔር ቤት ግንባታ አንድ ድንጋይ ነው። ድጋፍዎን በጸሎትዎ ደግሞ ያጅቡልን።
ይህ የገንዘብ ማሰባሰቢያ በቤተክርስቲያኑ አመራር ፈቃድ የሚካሄድ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ።
በTelebirr፣ በባንክ ወይም በካርድ ወዲያውኑ ይክፈሉ። (ክፍያው በChapa የተጠበቀ ነው)
ከላኩ በኋላ ስምዎን እና መጠኑን በ"ያግኙን" ፎርም ያሳውቁን።